ዱሮሊባል የሚችል ዓመት ነው። የያኔዋ ኢትዮጵያ በንግስተ ነገስታት ዘውዲቱ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ስር ስትሆን አዲስ አበባም ገና አሰርታት ያልደፈነች ወታት ነበረች። ፈረንጆቹ
ቱኩልየሚሏቸው የሳር ጎጆ ቤቶቻችን በብዛት የተቸመቸሙባት የያኔዋ አድስ አበባ ዘመናዊነት፣ የሥልጣኔ ብርሃን፣ አዲስ እድገት፣ ...የሚባሉ ነገሮችን ማስተናገድ መጀመሯ ነው። መንገዶች ተቀይሰዋል፣ መኪኖች ብቅ ብለዋል፣ ዘመናዊ የቤት አሰራሮች ታይተዋል፣ ጋዜጣ መታተም ጀምሯል ተማሪ ቤቶች ተከፍተዋል፣ ባቡርም እየተመመ ነው፣ ወዘተርፈ። እና፣ እንዲህ መባል በተጀመረበት በዚያን ጊዜ በአዲስ አበባ ከተከናወኑ ዘመናዊ ጉዳዮች አንዱ በመኪና ተጠምቆ በጠርሙስ እየታሸገ የሚሸጥ
ጠላየሚያዘጋጅ ፋብሪካ መቆሙ ነው።"መቼም "አይ ስልጣኔ!" ሳይባልለት አልቀረም። እርግጥ ስለፋብሪካ ነገር፣ በአውሮፓና በአሜሪካ ስለሚሠሩ ልዩ ልዩ ስራዎች በደንብ የሚያውቁ የሉም ማለት አይደለም። ለብዙዎች ግን በራሳቸው ምድር እንዲህ ዓይነት ተግባር መታየቱ የሚያስደምማቸው ቢሆን አይገርምም። የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ መስራችና ባለቤት ሙሴ ዳዊት ሃል የተባሉ የቤልጂግ ዜጋ መሆናቸውን የፋብሪካው መረጃዎች ያመለክታሉ። አንዳንድ የፅሁፍ መረጃዎች ደግሞ ባለቤቱ ጀርመናዊ የሆነ ኩባንያ እንደሆነ ይገልፃሉ። ከ43 ዓመታት በፊት በ1952 (እ.ኢት.አ) በታተመው የኢትዮጵያ የንንግድ ጆርናል የሚከተለው ሰፍሮ ይገኛል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ 20000 ካሬ ሜትር በሆነ ቦታ ላይ ሰፍሮ ይገኛል። ቢራ ፋብሪካው ከ36 ዓመት በፊት በአንድ የጀርመን ኩባንያ የተመሠረተ ሲሆን ከስድስት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያዊ የሆነ ኩባንያ ተረክቦታል። Ethiopian Trade Journal, Vol.1, No.1, August 1960:21 እርግጥ ፋብሪካው የተመሰረተው በሙሴ ዳዊት ሃል ሲሆን እኚህ ሰው ወደ በኋላ ለአንድ የጀርመን ኩባንያ ሸጠውታል። ፋብሪካው የተቆረቆረው በዚያው ዛሬ በቆመበት ስፍራ ነው። በንጉሰ ነገስቱ ማርሻል ሽሙት ጎዳና ተብሎ ነበር የሚታወቀው። ጎላ ጎላ ያለና ለዓይን የሚሞላ ህንፃ አዘጋጅቶ ስራውን ሲጀምር በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት የመጀመሪያ ምዕራፍ ከፋች ከሆኑት ጥቂት ኢንዱስትሪዎች አንዱ ለመሆን በቅቷል። ፋብሪካው ስራ ሲጀምር አብዛኛው የስራ ሂደት የሚከናወነው በሰው ቀጥተኛ ጉልበት በእጅና በእግር በሚዘወሩ መሳሪያዎች ነበር። ጥሬ ዕቃዎችን ከማጓጓዝና ወደ ቋት ከማስገባት ጅምሮ ድፍድፉን የማብላላቱ፣ የቢራ ገብሱን የመቀቀሉ፣ ቢራውን የማጣራቱና የማጥለሉ፣ የተጣራውን ቢራ በጠርሙስ እየሞሉ የማሸጉ፣ ወዘተርፈ ተግባራት ሁሉ የሰራተኞችን ቀጥተኛ ጉልበት የሚፈልጉ ነበሩ። የቢራ መሰረታዊ ግብዓቶች የሆኑት ቢራ፣ ገብስና የቢራ ጌሾ ከውጭ አገሮች ነበር የሚቀርቡት የፋብሪካውን የበላይ ማኔጅመንትና የጠመቃውን ሂደት የሚቆጣጠሩ የቴክኒክ ባለሙያዎችም እንኳን ባእዳን ዜጎች ነበሩ። በመጀመሪያዎቹ የምርት ዓመታትም በቀን ይመረት የነበረው 200 ያህል ጠርሙስ ቢራ እንደሆነ ይነገራል። በዚያን ዘመን በአዲስ አበባ የመጠጥ ቤቶች አልተስፋፉም፣ ኅብረተሰቡ በየቤቱ የሚጠመቅ ጠላና ጠጅ ይጠጣ እንደሁ እንጂ እንደዚህ እንዳሁኑ ዘመን መጠጥ ለመጠጣት ተብሎ የሚኬድባቸው ቦታዎች አልነበረም። የቀድሞውን ሁኔታ ሰምተናል የሚሉ አንጋፋ ሰራተኞች እንደሚጠቁሙት በመጀመሪያዎቹ ዓመታት የቢራ ምርቱ ይቀርብ የነበረው ለቤተመንግስቱ መኳንንት ነበር። ፋብሪካው በዚህ ሁኔታ ስራውን ቀጥሎ ሳለ ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ወረረች፡፡ አንዳንድ እርግጠኛ ያልሆኑ መረጃዎች በዚህ ወቅት ፋብሪካው ተዘግቶ እንደነበር ይገልፃሉ።
... በዚያን ጊዜ እንዳሁኑ በኤሌክትሪክ ኃይልና በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ ቦይለሮች አልነበሩም። ለሙቀት ክፍሉ የእሳት ማንደጃ የሚማገደው ግንዲላ በጥም ከባድ ሲሆን፣ በተለይ በሚማገድበት ጊዜ የእሳቱ ወላፈን እጅግ ኃይለኛ በመሆኑ እስከ ሶስት ሜትር ድረስ ቃጠሎው ይሰማን ነበር። በዚያን ጊዜ አጠቃላይ የፋብሪካው ሥራ ሙሉ በሙሉ በሰው ጉልበት ስለሚከናወን ስራው እጅግ አድካሚና አስቸጋሪ ነበር። ለጠመቃ የሚውል ኩንታል ገብስ ተሸክሞ ፎቅ መውጣት፣ ለመቅጃ ክፍል የሚቀርበውን ባዶ ጠርሙስ ከማጠብ ጀምሮ ታሽጎ እስኪወጣ ድረስ ከቦታ ቦታ የማጓጓዝና ሌሎችም የምርት ተግባሮች ሁሉ የሚከወኑት በሰው ኃይል በሸክም ብቻ ነበር። ሰራተኞች ወደመደበኛ ስራቸው ሳይሰማሩ በፊት በነፍስ ወከፍ አስራ አምስት ኩንታል ገብስ እየተሸከሙ ፎቅ በመውጣት ለወፍጮ በየቀኑ ማቅረብ የዕለት ግዳጃቸው ነበር። በዚያን ጊዜ ቢራው ወደ እያንዳንዱ ጠርሙስ የሚሞላው በሰው ኃይል በሚሽከረከር ባለአምስት ጡት መቅጃ ነበር። ቆርኪም በሰው እጅ በሚንቀሳቀስ መሳሪያ ይከደናል። ጠርሙስ የሚታጠበው በገንዳ ተዘፍዝፎ አድሮ በብሩሽ እየተፈገፈገ ነበር። ..."በዚህ ሁኔታ ምርቱን የቀጠለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ በ1966ቱ አብዮት መዳረሻ በመሳሪያዎቹ ደረጃ፣ በተሽከርካሪዎች አገልግሎት፣ በህንፃዎች፣ እንዲሁም በሽያጭ አውታሮች ስፋት መልካም አቋም ነበረው። ፋብሪካውን ለማስፋፋትና ተጓዳኝ የለስላሳ መጠጥ ምርት ለመጀመርም አቅዶ ነበር። ፋብሪካው በ1966 ወደመንግስት ይዞታነት እንዲዛወር ተደረገ። ይህ በፋብሪካው አሰራር ላይ አንዳንድ ችግሮችን ቢፈጥርም አንዳንድ መልካም እርምጃዎችን እና መሻሻሎችን አሳይቷል። በተለይ በሰው ኃይል አቅሙና አስተዳደር ረገድ ዓይነተኛ እድገት አስመዝግቧል። በምርት አቅጣጫም በ1969 በአገሪቱ ተወዳጅ የሆነውንና ሰፊ ገበያ ያለውን የድራፍት ቢራ አገልግሎት ለመጀመር ችሏል። ፋብሪካው በመንግስት ይዞታ ስር በነበረ ጊዜ የፋይናንስና አስተዳደራዊ ችግሮች ስለነበሩበት በዓለም ደረጃ ከ1970ዎቹ ወዲህ በቢራ ተመቃ ቴክኖሎጂ በኩል የተገኙ ፈጥን ርምጃዎችን ተከትሎ ለመጓዝ አዳግቶት ቆይቷል። የፋብሪካው ስያሜም ተቀይሮ ነበር። በ1970ዎቹ ዓመታት አንድ ጊዜ
ፒልስነር ቢራ ፋብሪካተብሎ ነበር። ፋብሪካው እነዚህን የመሰሉ ችግሮች ቢያጋጥሙትም፣ በሌላ በኩል ደግሞ የፋብሪካው ስምና ምርት ተወዳጅ ሆኖ እንዲቀጥል ለማደረግ ችለዋል። የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ፣ በማበረታታትና በማጎልበት ፋብሪካው የተጫወተው ሚናም ከፍተኛ ነው።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ | ኮምቦልቻ | ካስቴል ዋይነሪ | ሀዋሳ ቢራ | ድምር | |
ቋሚ | 523 | 367 | 99 | 243 | 1232 |
ጊዜያዊ | 228 | 233 | 774 | 250 | 1485 |
ድምር | 751 | 600 | 873 | 493 | 2,717 |
የታክስ ዓመት | 2009 | 2010 |
ኤክሳይዝ ታክስ | 254 | 367 |
ተጨማሪ እሴት ታክስ | 232 | 233 |
የትርፍ ታክስ | 138 | 600 |
ከስተምስ /Customs Duty/ | 36 | 600 |
ሱር ታክስ | 32 | 600 |
ድምር | 692 | 600 |
2009 | 1,548,000,000 |
2010 | 1,676,000,000 |
ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ ኃላ.የተ.የግ.ማህ (ኢንዱስትሪ)
Addis Ababa, Ethiopia
GPS: Lat 9.011666 / Lon 38.742482
Remark: Other businesses who are partnering with AddisMap, do not require such a payment by you.
Once you send your request and payment, the AddisMap team will contact the business owner on your behalf and reply to you via email usually within a business day. This is useful if you do not speak Amharic - you send your request in Englisch, AddisMap will translate. For complicated requests - for example if paper work is needed - AddisMap might request additional funds.