ኢትዮጵያ - Garmin and Mobile Phone GPS Map Downloads

Buy now

ለዚህ ፕሮግራም መክፈልዎ ኢትዮፕያን በካርታ ላይ የማስቀመጥ ሂደቱን ይደግፋሉ በቀጠይነት የምናወጣቸውን የማሻሻያ እትሞች የሚያገኙበት አድራሻ በኢ-ሜይል ይደርስዎታል

Exclusive: Contains more than 1500 additional points of interest.

Limited time offer: Now 25% discount!

Pay via Paypal

Garmin Navigation Devices

Last updates

ማውረጃዎች

የጋርሚን ካርታው በሁለት ዓይነት መልኩ ተዘጋጅቷል የኢትዮጵያን እና አዲስ አበባ ዘርዘር ባለ መልኩ ከበርካታ የድርጅቶች መገኛ ጋር በማካተት ከሌሎች ካርታዎች የተሻለ መረጃ ይዟል

የጋርሚን GMAPSUPP ምስል

ይህ ፕሮግራም የተሰራው USB ላላቸው ጋርሚን መሳሪያዎች ነው በሁሉም ሲስተሞች ላይ ይሰራል (Windows, Linux, MacOS) ነገር ግን ፕሮግራሙን ለሚቀበሉ አዳዲስ የጋርሚን እትሞች ነው
  1. የጋርሚን መሳሪያችሁን ከኮምፒዩተሩ ጋር በUSB አገናኙ
  2. የፋይል መጎብኛችሁን ክፈቱ
  3. gmapsupp.img የሚለውን ፋይል ኮፒ አድርጉ እና "ጋርሚን" ወደሚለው የፋይል ማህደራችሁ ገልብጡ
  4. በመቀጠልም መሳሪያዎን በጥንቃቄ ይንቀሉ

የአዲስ ማፕ የጋርሚን MAPSOURCE መጫኛ

እነዚህ አካሄዶች የሚሰሩት በማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ከService Pack 3ጅምሮ ነው የMAPSOURCE ሶፍትዌር መጫኛ ከሌለዎት ከታች በተገለፀው መንገድ መጫን ይችላሉ MAPSOURCE ከተጫነልዎት በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ይኖርብዎታል
  1. AddisMap.exeን ያስጀምሩና የመጫኛውን የአካሄድ ቅደም ተከተል ጠብቀው ይሂዱ
  2. MAPSOURCEን ይክፈቱ
  3. ከላይ ባለው በስተግራ ሳጥን ውስጥ ይግቡና "AddisMap"ን ይምረጡ
  4. ሜኑው ውስጥ "Tools->Map"ን ይጫኑ
  5. የማጉሊያ መነፅር ምልክቱን "-" በመጠቀም ሙሉ ኢትዮጵያ እስከሚታይዎ ድረስ ምስሉን ያርቁት
  6. በማውስዎ በመጠቀም በኢትዮጵያ ካርታ ላይ አራት መዓዘኑን ይሳሉ
  7. የጋርሚን ጂ.ፒ.ኤስ. መሳሪያዎን ያገናኙት
  8. ሜኑው ውስጥ "Transfer->Send to Device" የሚለውን የጫኑት

የጋርሚን MAPSOURCEመጫኛ

MAPSOURCE ከጋርሚን የንግድ ካርታዎች ጋር ተያይዞ የሚገኝ ነው የዚህ ዓይነት ካርታ ከሌለዎት የMAPSOURCE ማሻሻያውን እንዲሁም የማሰልጠኛ ማዕከሉን ከዚህ በማውረድ መሰረታዊ ካርታውን ያግኙ እነዚህን ቅደም ተከተሎች በጥንቃቄ ይከተሉ
  1. የ UNZIP ሶፍትዌር ያስፈልግዎታል እኛ የምንመክረው ነፃ የሆነውን 7ZIPን ነው ከ7-zip.org በመሄድ መጫን ይችላሉ
  2. የማሰልጠኛ ማዕከሉን ያውርዱ
  3. የማሰልጠኛ ማዕከል ሶፍትዌሩን ይጫኑ
  4. የMAPSOURCE ሶፍትዌሩን ያውርዱ
  5. .exe ያለው ፋይል ላይ የቀኝ ክሊክ ያድርጉ እና "Extract to Folder"የሚለውን ይምረጡ
  6. የተዘረዘረውን የፋይል ማህደር ይክፈቱ
  7. በአዲሱ የፋይል ማህደር ውስጥ MSmain.msi ላይ ሁለት ጊዜ ክሊክ ያድርጉ
  8. ትንሽ ይጠብቁ
  9. setup.exe ላይ ክሊክ ያድርጉና ቅደም ተከተሎቹን ይከተሉ
እንኳን ደስ አለዎ MAPSOURCEን ጭነዋል አሁን ከላይ ያሉትን ቅደም ተከተሎች በመጠበቅ AddisMapን መጫን ይችላሉ

የተንቀሳቃሽ ስልክ ካርታ

Tested on the following phones
  1. Nokia 6303 classic